የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ የምግብ ደህንነት ላብራቶሪ ተከፈተ

By Meseret Awoke

April 14, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የምግብ ደህንነት ዘመናዊ ላቦራቶሪ በዛሬው እለት በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምሯል፡፡

አዲሱ ላቦራቶሪ የውሃ ወለድ እና የውሃ ወለድ ወረርሽኝ ላይ ትኩረት አድርጎ ምርመራ ያካሂዳል፡፡

ላቦራቶሪውን ለመገንባት 7 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ መግለጻቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የምግብ ሳይንስ እና ኒዉትሪሽን ዳይሬክቶሬት፣ በዘመናዊ መልኩ የተሰራ የምግብ ደህንነትና የምግብ ማይክሮ ባዮሎጂ የምርምር ኬዝቲም ላብራቶሪ የኢንስቲትዩቱ ዋና እና ምክትል ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን