አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 92 ኢትጵያውያን ዜጎች ከየመን መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በየመን የሚገኙ ዜጎች ወደ አገራቸው ለመመለስ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀን የተውጣጣ የልዑካን ቡድን ወደ ኤደን በመሄድ የጉዞ ሰነድ የመስጠት ስራ መከናወኑንም ተጠቅሷል።
በዚህ መሰረትም ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ዛሬ የተመለሱት፡፡
በወቅቱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በትናትናው ዕለትም 160 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ድጋፍ ከየመን ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው የሚታወስ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን