የሀገር ውስጥ ዜና

በጎንደር ከተማ 168 ህገወጥ ሽጉጦች ተያዙ

By Meseret Demissu

April 13, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) በጎንደር ከተማ 168 ህገወጥ ቱርክ ሰራሽ  ሽጉጦች መያዙን የጎንደር ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

በመምሪያው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር እየሩስ አስማረ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ ህገወጥ የጦር መሳሪያው የተገኘው በተለምዶ ህዳሴ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግለሰብ ቤት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ነው፡፡

የመኖሪያ ቤቱ  ባለቤት ለጊዜው የተሰወሩ ሲሆን ግለሰቧን ለመያዝና የህገወጥ የጦርመሳሪያውን  ምንጭ ለማወቅ ፖሊስ እየሰራ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር እየሩስ አስማረ  ገልጸዋል።

በሹመት አለማየሁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን