አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ1442 ኛው የረመዳን ፆም ነገ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ገለጸ።
ምክር ቤቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት እንደገለጸው÷ ህዝበ ሙስሊሙ በፆምና ጸሎት የሚየሳልፈው የረመዳን ወር ነገ የሚጀምረው ጨረቃ ዛሬ በመታየቷ ነው።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድሪስ ÷ወሩን በመረዳዳት በመተሳሰብና ከምንም በላይ ለሰብአዊነት ቅድሚያ በመስጠት ህዝበ ሙስሊሙ እንዲያሳልፍ ጥሪ አቅርበዋል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን