የሀገር ውስጥ ዜና

በከተማዋ የአርሶ አደር መንደሮች የተደራሽ የጠጠር መንገድ ግንባታዎች ተጀመሩ

By Meseret Awoke

April 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በከተማዋ የዕለት ተዕለት ኑሮ አስቸጋሪ ያደረገውን የመንገድ ችግር ለመቀየር ፣ ለትራፊክ ፍሰት አስተዋጽኦ የሚኖራቸው የአርሶ አደር መንደሮች የተደራሽ የጠጠር መንገድ ግንባታዎች ተጀምረዋል።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ 13 ኪሎ ሜትር የአርሶ አደር መንደሮች የተደራሽ የጠጠር መንገድ ስራ ፕሮጀክት አስጀምረዋል።

ከአዲስ አበባ ከተማ ዕድገትና ከነዋሪዎቿ ፍላጎት ጋር የሚጣጣም የመንገድ ልማት ያስፈልጋል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፤ ፕሮጀክቱ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ አርሶአደሮችን ምርታቸውን ያለምንም ውጣ ውረድ ለገበያ ለማቅረብ ያግዛል ብለዋል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ በአፋጣኝ እንዲጠናቀቅ የከተማ አስተዳደሩ ቀን ከሌት እንደሚሰራና የአካባቢው አርሶአደሮች አደሮች አስፈላጊውን እገዛ እና ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸውም ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ በበኩላቸው ዛሬ ግንባታው የተጀመረውን መንገድ ጨምሮ በአምስቱ የማስፋፊያ ክፍለከተሞች በጠቅላላው ከ36ኪሎ ሜትር በላይ የጠጠር መንገድ ግንባታ እንደሚካሄድ ገልጸዋል ።

ከከተማው ፕረስ ሴክሬታሪ ጽህፈት ቤት ባገኘነው መረጃ ለእነዚህ መዳረሻ መንገዶች የከተማ አስተዳደሩ ከ151 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መመደቡን ኢንጂነር ሞገስ ተናግረዋል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!