የሀገር ውስጥ ዜና

ከአቃቂ ጥልቅ ጉድጓዶች ወደ ከተማ ውሃ ይዞ የሚመጣው 800 ሚሊ ሜትር ከባድ የውሃ መስመር ላይ ስብራት አጋጥሟል

By Meseret Awoke

April 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከአቃቂ ጥልቅ ጉድጓዶች ወደ ከተማ ውሃ ይዞ የሚመጣው 800 ሚሊ ሜትር ከባድ የውሃ መስመር ስብራት እንዳጋጠመው ተገልጿል፡፡

ስብራቱም ትላንት ምሽት ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅጥር ግቢ ውስጥ በግንባታ ምክንያት ያጋጠመ ሲሆን ፤ ጥገና ለማከናወን ርብርብ እየተደረገ ነው ።

በመሆኑም ከትላንት ሚያዝያ 2 እስከ ዛሬ ምሽት ድረስ መስመር ተዘግቶ ጥገና የሚከናወን ይሆናል፡፡

በመሆኑም አለም ባንክ፣ ቤቴል፣ አየር ጤና፣ ጀሞ አካባቢ በከፊል ፣አንፎ ቀራኒዮ፣ ጦርሀይሎች፣ልደታ መልሶ ማልማት ፣ሳር ቤት፣ ሜክሲኮ፣ ጀሞ ሚካኤል ፣ ጀርመን አደባባይ ውሃ ተቋርጧል፡፡

ባለስልጣኑ የተሰበረውን ከፍተኛ የውሃ መስመር በአጭር ጊዜ ለመጠገን ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን፤ በዚህ አጋጣሚ በተጠቀሱት አከባቢዎች እስከ አርብ ስርጭቱን ይቆራረጣል። በዚህም በተጠቀሱት አካባቢዎች የውሃ እጥረት ስለሚከሰት ደንበኞች ችግሩን ተረድተው እንዲታገሱ ጠይቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!