የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ለጂቡቲው ፕሬዚደንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

By Meseret Awoke

April 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት እስማኤል ኦማር ጊሌ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዚደንት ኦማር ጊሌ በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎና ድምጽ ፕሬዚደንታዊ ምርጫን በማሸነፋቸው ፕሬዚደንት ሳህለ ወርቅ ልባዊ ደስታቸውን ገልጸዋል።

‘‘ለእርሳቸውና ወንድም ለሆነው የጂቡቲ ሕዝብ መልካሙን ሁሉ ተመኝቻለሁ’’ ሲሉም በትዊተር ገጻቸው መልዕክታቸውን አስፍረዋል፡፡

የጂቡቲው ፕሬዚደንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በአገሪቷ ለ5ኛ ጊዜ በተከናወነው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፋቸው ይታወቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!