የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ  ለጁቡቲው ፕሬዚዳንት የደስታ መግለጫ አስተላለፉ

By Meseret Demissu

April 10, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  አሕመድ ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ  በሀገራቸው በተደረገው ምርጫ በድጋሜ ማሸነፋቸውን ተከትሎ የደስታ መግለጫ አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  በቲውተር ገጻቸው ላይ ÷ወንድሜ ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ  እንኳን ደስ አለህ ብለዋል።

አያይዘውም ኢትዮጵያ ለእርስዎ እና ለታላቁ የጅቡቲ ህዝብ ብልጽግናን ትመኛለች ብለዋል።

ወደፊትም ኢትዮጵያ የጅቡቲ ቋሚ  ወዳጅ እና ጎረቤት ሆና ትቀጥላለችም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡