የሀገር ውስጥ ዜና

ሩሲያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በሳይቤሪያ አየር ክልል እንዲበር ፈቃድ ሰጠች

By Tibebu Kebede

April 09, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በሳይቤሪያ አየር ክልል እንዲበር ፈቃድ መስጠቷን በኢትዮጵያ የሀገሪቱ ኤምባሲ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ እና ሩሲያ አየር መንገድ ባለስልጣናት በደረሱት ስምምነት መሰረት በረራው መፈቀዱ ተጠቁሟል።

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እቃ ጫኝ አውሮፕላን የሳይቤሪያ አየር ክልል የሚጠይቀውን መስፈርት በሟሟላት የአየር ክልሉን መጠቀም ይችላል ተብሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!