አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ መቀመጫቸውን ግብጽ አድርገው ኢትዮጵያን ጨምሮ ሱዳን እና ቱርክን ኢላማ አድርገው መረጃ ሲያሰራጩ ነበሩ ያላቸውን አካውንቶች መዝጋቱን አስታወቀ።
አካውንቶቹ ከ300 ሺህ በላይ ተከታዮች እንዳላቸውም ነው ኩባንያው የገለጸው።
በዚህም ኩባንያው 17 የፌስቡክ አካውንት፣ 6 ገጾችና እና 3 የኢንስትግራም አካውንቶችን መዝጋቱን ነው የገለጸው።
ኩባንያው ባደረገው ምርመራ የፌስቡክ እና ኢንስታግራም ገጾቹ መቀመጫውን ግብፅ ያደረገ ቢ ኢንተራክቲቭ የተባለ ማርኬቲንግ ኩባንያ አካል መሆናቸውንም ነው ያስታወቀው።
ኩባንያው አክሎም አካውንቶቹ ሲያሰራጩ የነበረው በኢትዮጵያ በስፋት በሚነገው አማርኛ ቋንቋ ነው ሲል ገልጿል።
ይዘቱም ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በገነባችው ግዙፍ ግድብ ላይ ያነጣጠረ ነው ብሏል።
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
115
Engagements
Boost Post
99
5 Comments
11 Shares
Like
Comment
Share