የሀገር ውስጥ ዜና

አንጋፋው ድምፃዊ እና የዜማና ግጥም ደራሲ አየለ ማሞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

By Tibebu Kebede

April 07, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው ድምፃዊ እና የዜማና ግጥም ደራሲ አየለ ማሞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

አርቲስት አየለ ማሞ ከዜማና ግጥም ደራሲነቱ ባለፈም የማንዶሊኑ ንጉስ በመባል ይታወቃል፡፡

የቀብር ሥነ ሥርዓቱም በነገው እለት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ይፈፀማል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርቲስት አየለ ለአንጋፋ ድምጻውያን በርካታ ዜማዎችን ሰርቶ ከመስጠት ባለፈ ካሊፕሶ በሚለው ሙዚቃ በህዝብ ዘንድ ይበልጥ ይታወቃል፡፡

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥም ከ1950ዎቹ ጀምሮ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረከተ አንጋፋ ባለሙያ ነበር፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!