ኮሮናቫይረስ

በኮቪድ19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር የጤና አገልግሎቱ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ነው – የጤና ሙያ ማህበራት

By Abrham Fekede

April 07, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሙያ ማህበራት በኮቪድ19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መሄዱ የጤና አገልግሎቱ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እንደሚሆን አመላካች መሆኑን አስታወቁ።

የጤና ሙያ ማህበራት በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በኮቪድ19 የሚያዙ እና ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፡፡

ይህን በማስመልከት በመግለጫቸው ከአሁን ቀደም በሌሎች ሀገራት የተከሰተውን በፈጣን መንገድ ይሰራጫል ተብሎ የሚታመነው አዲስ የኮቪድ ልውጥ ሕዋስ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባበት እድል ሊኖር ስለሚችል ጥናት ሊደረግበት እንደሚገባ ምክረ ሀሳባቸውንም አቅርበዋል።

የኮቪድ19 ስርጭትን ለመግታት ሲደረጉ የነበሩ ጥንቃቄዎች በመዘንጋታቸው አሁን ለደረስንበት አሳሳቢ የስርጭት መጠን ምክንያት ነው ብለዋል።

የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ተከታታይነት ያላቸው የግንዛቤ እና የቁጥጥር ሥርዓት ሊዳብር እንደሚገባ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!