ኮሮናቫይረስ

በብራዚል በኮቪድ19 ምክንያት በአንድ ቀን 4 ሺህ 195 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

By Abrham Fekede

April 07, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በብራዚል አዲስ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ በአንድ ቀን ብቻ 4 ሺህ 195 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ፡፡

በሀገሪቱ የሚገኙ ሆስፒታሎች በወረርሽኙ በተያዙ ሰዎች መጨናነቃቸው ተነግሯል፡፡

በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነው የጽኑ ህሙማን ክፍል ኮቪድ19 በተያዙ ህሙማን መያዙንም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

እስካሁን 337 ሺህ ብራዚላውያን ዜጎች በወረርሽኙ ምክንያት ለሕልፈት ተዳርገዋል ተብሏል፡፡

ሆኖም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ ማንኛውንም ክልከላ እና ገደብ ባለመጣል መጽናታቸው ነው የተገለጸው፡፡

ምክንያታቸውም ቫይረሱ ከሚያደርሰው ጉዳት ይልቅ ኢኮኖሚው ይጎዳል ብለው ማመናቸው ነው ተብሏል፡፡

እስከሁን በብራዚል 92 ዓይነት የኮሮና ቫይረስ ሕዋሶች መገኘታቸውን ባለሙያዎች የጠቀሱ ሲሆን አንዳንዶቹ በፍጥነት የሚዛመቱ ናቸው ተብሏል፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!