Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች በትምህርት ቤቶች እንዲጠናከሩ የሚያስችል ስምምነት ተደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲጠናከር ለማድርግ የሚያስችል ስምምነት ተደረገ።

ስምምነቱ  በትምህርት ሚኒስቴርና በፌደራል ስፖርት ኮሚሽን መካከል ነው የተደረሰው።

የሰውነት ማጎልመሻና ስፖርት ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ የትምህርት ተቋማት የሰውነት ማጎልመሻና ስፖርት ትምህርት አደረጃጀት፣ የስፖርት ማዘውትሪያ ስፍራዎች ግብኣት ዝግጅት፣ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጥና ፕሮጀክት፣ የስፖርት ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ስልጠና፣ የስፖርታዊ ውድድሮች መርሃ ግብር ዝግጅት እና የትምህርት ማህበረሰብ ስፖርት ተሳትፎ የስምምነቱ አካል ናቸው ተብሏል።

በሁሉም የትምህርት ተቋማት ውስጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ለማስፋፋት የሚያስችለውን ይህንን ስምምነት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ እና የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ተፈርሟል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ንቁና ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ስፖርትና ትምህርት ተነጣጥለው መታየት የለባቸውም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ትምህርት ቤቶችን ለተማሪዎች ምቹ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር በበኩላቸው፣ ስምምነቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረጊያ ቦታዎች በትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉ ለማድረግና መልካም ዜጋን ለማፍራት አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ መናገራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version