አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ 5ተኛ ሳምንት የፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተካሄደ።
አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ እና ጽዱ ከተማ ለማድረግ “አካባቢዬን በማፅዳት ለከተማዬ ውበት አምባሳደር ነኝ” በሚል ነው የፅዳት ዘመቻው በዛሬው ዕለት የተካሄደው።
የከተማዋ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር እሸቱ ለማ ሁሉን አቀፍ የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄዎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ ከብሎክና ከሁሉም ነዋሪዎች አደረጃጀት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
በየሳምንቱ በሚካሄደው በዚህ የጽዳት ዘመቻ ከ35 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መሳተፋቸውን ነው ያብራሩት፡፡
ርዕሰ መዲናዋን ጽዱ ለማድረግም አበረታች ለውጥ እየታየ መሆኑንም ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
በጽዳት ዘመቻው የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!