በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ53 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአንድ ሳምንት ውስጥ 53 ሚሊየን 795 ሺህ 644 ብር የሚገመቱ ዕቃዎች በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጡ እና ወደ ሀገር ሊገቡ ሲሉ መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች 40 ሚሊየን 300 ሺህ 334 ብር የሚገመቱ ዕቃዎች ወደ ሀገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን፥ 13 ሚሊየን 4 መቶ 95 ሺህ 310 ብር የሚገመቱ ዕቃዎች ደግሞ ከሀገር ሊወጡ ሲሉ መያዛቸውን አስታውቋል።
የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ የጦር መሣሪያዎች፣ መድኃኒቶች፣ አደንዛዥ እፆች፣ የግብርና ምርቶች፣ ምግብ ነክ ሸቀጣሸቀጦች፣ አልባሳት እና ጫማዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመዋቢያ ምርቶችና የመለዋወጫ ዕቃዎች ከተያዙት መካከል ይገኙበታል ተብሏል፡፡
ከእቃዎቹ በተጨማሪም የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩ 35 ተሽከርካሪዎች መያዛቸውንም ገልጿል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!