የሀገር ውስጥ ዜና

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለቄራ አንበሳ ስፖርት ማህበር የትጥቅ ድጋፍ አደረጉ

By Tibebu Kebede

April 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ቄራ አልማዝዬ ሜዳ በመገኘት ለቄራ አንበሳ ስፖርት ማህበር የትጥቅ ድጋፍ አደረጉ ።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ዋልያዎቹ፣ ከተለያዩ ባለሀብቶች እና አርቲስቶች ጋር በመሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ቄራ አልማዝዬ ሜዳ በመገኘት ለቄራ አንበሳ ስፖርት ማህበር የትጥቅ ድጋፍ አድርገዋል ።

አልማዝዬ ሜዳ በርካታ ስፖርተኞችን ያፈራ ሜዳ መሆኑን የገለፁት ምክትል ከንቲባዋ በዘመናዊ መንገድ ግንባታው ይካሄዳል ብለዋል ።

ስፖርት ሰላምን ፣አንድነትን እና ወዳጅነትን በማጠናከር በኩል ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ አጠቃላይ ስፖርቱን ለማሳደግ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ቄራ እና አካባቢው የሚኖሩ ባለሀብቶች በበኩላቸው የአልማዝዬ ሜዳን ከንድፍ ጥናት ጀምሮ ሙሉ የሜዳውን ግንባታ ለማካሄድ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን ለመቆም ቃል ገብተዋል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!