የሀገር ውስጥ ዜና

አንጋፋው ጋዜጠኛ ከተማ ሀይለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

By Tibebu Kebede

April 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው የኢቢሲ ጋዜጠኛ ከተማ ሀይለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

ጋዜጠኛ ከተማ ሀይለማርያም በቀድሞው የኢትዮጵያ ሬዲዮ በአሁኑ ኤፍ ኤም አዲስ 97 ነጥብ 1 ለረጅም አመታት አገልግሏል፡፡

ከተማ ሀይለማርያም ባደረበት ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንት ሌሊቱን በተወለደ በ45 አመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

የጋዜጠኛ ከተማ ሀይለማርያም የቀብር ስነስርዓት ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።

ጋዜጠኛ ከተማ ሀይለማርያም ባለትዳርና የአንድ ወንድ እና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበር፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ባልደረቦቹ እና አድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!