የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት ሰባት ቀናት 14 ሺህ 437 ግለሰቦች በኮቪድ19 ተይዘዋል

By Tibebu Kebede

April 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሰባት ቀናት ከመጋቢት 17 እስከ መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 14 ሺህ 437 ግለሰቦች በኮቪድ19 መያዛቸው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታወቀ፡፡

የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 100 ግለሰቦች ውስጥ 25ቱ ቫይረሱ እንደተገኘባቸውም ኢንስቲቲዩቱ ገልጿል፡፡

በዚህ ጊዜ ውስጥም 149 ግለሰቦች ህይወታቸውን አጥተዋልም ነው ያለው፡፡

በትናንትናው እለት ለ8 ሺህ 294 ግለሰቦች የላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ 2 ሺህ 372 ሰዎች ኮቪድ-19 ሲገኝባቸው ይህም ከ100 ሰዎች 29ኙ ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ ያሳያል ነው ያለው፡፡

አሁን ላይም የቫይረሱ ስርጭት በመላ ሃገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንም ነው ኢንስቲቲዩቱ የገለጸው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ህብረተሰቡም ሆነ መንግስታዊ አካላት የወጡ መመሪያዎችን በመተግበርና በሃላፊነት ስሜት በመንቀሳቀስ የቫይረሱን ስርጭት እንዲከላከሉም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!