Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናይጄሪያ ‘ምርጡ አየር መንገድ’ ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናይጄሪያ ‘ምርጡ አየር መንገድ’ ተባለ።
በናይጄሪያ የድንቆች ኤክስፖ ማገባደጃ ላይ ለተቋማት በተሰጠ እውቅና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ‘የምርጥ ዓለም ዓቀፍ ሽልማት’ አሸናፊ ሆኗል።
የአየር መንገዱ የትራፊክና ሽያጭ ስራ አስኪያጅ ሰናይት አታክልት ሽልማቱን ከትሪኒዳድና ቶቤጎ እና ከጃማይካ አምባሳደሮች እጅ ተቀብለዋል።
አየር መንገዱ ለአገልግሎቱ ዕውቅና በመሰጠቱም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ያለፈው ዓመት ፈታኝ እንደነበር ያስታወሱት ሰናይት አታክልት አየር መንገዱ ፈተናውን ለማለፍ የጭነት አገልግሎት በመስጠት የወደፊት እጣ ፈንታውን ብሩህ ማድረጉን ገልጸዋል።
የጭነት ማጓጓዝ ላይ ትኩረት ማድረግ ከተጀመረበት ያለፈው አንድ አመት ጀምሮ የዓለም የምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ ከሌሎች አጋሮች ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ አሊባባ ፋውንዴሽን፣ የአለም ጤና ድርጅት እና ለጋሽ አገሮች ለአፍሪካ የሰጡትን የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁሶችን በውጤታማነት ታጅባ ማሰራጨት መቻሏን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version