አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ንፁሀን ዜጎችን በማንነታቸው እየለዩ ጥቃት በሚፈፅሙ ፅንፈኛ ቡድኖች ላይ የፌዴራልና የክልል መንግስታት ሕግ እንዲያስከብሩ የአማራ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ጠይቀዋል።
የክልሉ መንግስት ርዕሠ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ዞን እና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ማንዱራ ወረዳ በዜጎች ላይ እየደረሠ ያለውን ጥቃት አስመልክተው መግለጫ ሠጥተዋል።
የክልሉ መንግስት ማንነትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ በፅንፈኞቹ ኦነግ ሸኔ እና የጉምዝ አማፂ ቡድኖች በህፃናት፣ ሴቶች እና ንፁሀን ላይ እየደረሠ ያለው የሠብአዊ መብት ጥሠት እንደሚያወግዝም ርዕሠ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
የአማራ ህዝብ በሀገረመንግስት ግንባታው በነበረው ሚና በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ይኖራል ያሉት ርዕሠ መስተዳድሩ በማንነቱ የሚደርሠው ግፍ ሀገርን የመበተን ሴራ አካል ነው ብለዋል።
ሆኖም ህዝቡ እየሞተም በሀገሩ ተስፋ የማይቆርጥ ወንድማማችነትን የሚያስቀድም በየዘመናቱ የሴረኞችን ህልም እያመከነ የሀገር ዋልታነቱን ከመላው ብሄረሠቦች ጋር በመሆን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
የክልሉ መንግስትም በጉዳዩ ላይ ለመተባበርና መፍትሄ ለማምጣት በጋራ እንደሚሠራም መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!