Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ የደም ልገሳ አከናወነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ደሜን ለወገኔ ድምፄን ለብልፅግና በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ አከናወነ፡፡
በመርሃ ግብሩም 500 የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ አባላት ደም ለግሰዋል፡፡
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መልኬ አለማየሁ ሴቶች ከማጀት ባለፈ በፖለቲካውም ለውጥ ማምጣት ይችላሉ ብለዋል፡፡
በዚህም ሴቶች አባል ከመሆን ባለፈ በፖለቲካው ለውጥ እያመጡ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ፓርቲው የሰጠውን ዕድልም ሴቶች እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version