የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በመጪው ክረምት ከ6 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ ነው

By Abrham Fekede

April 01, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በመጪው ክረምት ከ6 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ገለጹ፡፡

አቶ ጥራቱ በየነ ከአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን አመራሮች ጋር በመሆን በእንጦጦ፣ ጉለሌ እና ሱስኒ ችግኝ ጣቢያዎች በመገኘት እየተደረገ ያለውን ዝግጅት ተመልክተዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በከተማዋ የተጀመረውን የአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብርን ለማስቀጠል በተለያዩ ችግኝ ጣቢያዎች ከ4 ሚሊየን በላይ ሃገር በቀል እና የፍራፍሬ ችግኞችን በማፍላት ስራ በማከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ከስድስት ሚሊየን በላይ ከሚሆኑት ችግኞች ውስጥ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ችግኞች ናቸው ብለዋል፡፡

ባለፈው ክረምት በአዲስ አበባ ከተማ 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ችግኞች መተከላቸው ይታወሳል፡፡

ከተተከሉት ውስጥ 83 በመቶዎቹ መጽደቃቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ማስታወቁን ከመዲናዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!