አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፋን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት ።
በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሰው ፣የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ፣ም/ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ እና ሌሎች የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝተው ቡድኑን አበረታተዋል ።
ብሔራዊ ቡድኑ በነገው ዕለት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ከአረፋበት ሆቴል ተነስቶ በአዲስአበባ በተመረጡ ዋና ዋና ጎዳናዎች ለህዝቡ ደስታቸውን ይገልፃሉ ፤ ህዝቡም ለብሔራዊ ቡድኑ ያለውን ድጋፍ እና አክብሮት የሚገልፅ ይሆናል መባሉን ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!