የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የምግብ ስርአት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

March 31, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የምግብ ስርአት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

መድረኩ በግብርና፣ በጤና ሚኒስቴር እና ባለድርሻ አካላት በትብብር የተዘጋጀ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

የምክክር መድረኩ በሃገሪቱ ወቅታዊ እና የወደፊት የምግብ ስርአት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን፥ በሀገሪቱ ዘላቂ እና ጤናማ አመጋገብን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችሉ መፍትሄዎች ይገኙበታል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!