Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ትናንት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጡት ምላሽ  ከአውድ ውጭ መወሰዱን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ትናንት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጡት ምላሽ ከአውድ ውጭ መወሰዱን አስታወቁ፡፡

 

መግለጫውን ተከትሎ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች በፌዴሬሽን ሊዋሃዱ ነው በሚል በዚህ ጉዳይ ላይ መንግስት ምን አቋም አለው የሚል ጥያቄ ቀርቦ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
 
ለቀረበው ጥያቄም የተሰጠው ምላሽ አንዳንድ መገናኛ ብዙኀን በተለየ አውድ ማቅረባቸውን ነው የገለጹት፡፡
 
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኤርትራውያን ወገኖች ጉዳዩ ከአውድ ውጭ መወሰዱን እንዲያውቁ አሳስባለሁ ብለዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለኤርትራ ሉዓላዊነት የማይናወጥ አቋም አላቸው ነው ያሉት፡፡
 
እኔም በግለሰብ ደረጃ የኤርትራን ሉዓላዊነት አከብራለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
 
ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለተፈጠረው ብዥታ ይቅርታ እጠይቃለሁ ማለታቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
Exit mobile version