የሀገር ውስጥ ዜና

የብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በከተማዋ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

By Abrham Fekede

March 31, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በከተማዋ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

ከፓርቲዎቹ መካከል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ፣ መኢአድ፣ የህዳሴ ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ህብረት፣ የአዲስ ትውልድ ፓርቲ እና የሌሎች የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ይገኙበታል፡፡

ከታላቁ ቤተመንግሥት የመኪና ፓርኪንግ በጀመረው የጉብኝት መርሐ ግብር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ስለ ፕሮጀክቱ ማስረዳታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡