የሀገር ውስጥ ዜና

ዳሽን ቢራ ለገበታ ለሀገር 25 ሚሊየን ብር ለገሰ

By Abrham Fekede

March 30, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት 25 ሚሊየን ብር መለገሱን አስታወቀ፡፡

ዳሽን ቢራ በጉዳዩ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫው ፋብሪካው ባለፉት 20 ዓመታት ለተለያዩ ልማቶች የሚውል 600 ሚሊየን ብር መለገሱንም አስታውሷል፡፡

ድጋፉ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት በቱሪዝም ዘርፉና በሀገር ገጽታ ላይ የሚያሳርፈውን አስተዋጽዖ ታሳቢ በማድረግ መሆኑንም ገልጿል፡፡

ዳሽን ቢራ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጫ ጠቅሷል፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!