አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ሀገራት ወደፊት ሊከሰት የሚችል ወረርሽኝን ለመከለከል የሚረዳ የዝግጁነት ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ፡፡
የጀርመኗ መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል፣ የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንና የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ጨምሮ ከ20 በላይ የሃገራት መሪዎች ናቸው ጥሪውን ያቀረቡት፡፡
መሪዎቹ ወቅታዊውን የዓለም የጤና ስጋት መነሻ በማድረግ ነው ጥሪውን ያቀረቡት ተብሏል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም ወደፊት ኮቪድ19ኝን የመሰሉ ወረርሽኞች መቼ እንደሚከሰቱ ስለማይታወቅ መከላከል በሚያስችል መልኩ ዝግጁነት ሊኖር ይገባል የሚል አቋም አላቸው፡፡
ለዚህ ይረዳ ዘንድ ወረርሽኞችን ቀድሞ ለመከላከል አሁን የትብብር ስምምነት መመስረት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ሃገራትም ይህን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ስምምነቱን ለመመስረት የሚደረገውን ሂደት እንዲቀላቀሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
እስካሁን ይህን የዝግጁነት ስምምነት 24 ሃገራት የፈረሙት ሲሆን፥ ከፈራሚዎቹ መካከል የዓለም ጤና ድርጅትም ይገኝበታል፡፡
ስምምነቱ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ በኋላ ለመልሶ ግንባታ ከተፈረመው ስምምነት ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ተጠቅሷል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!