የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ 300 ሺህ ሲኖፋርማ የኮቪድ19 ክትባት ከቻይና ተረከበች

By Tibebu Kebede

March 30, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ 300 ሺህ ሲኖፋርማ የኮቪድ19 ክትባት ከቻይና መንግስት ተረከበች።

በኢትዮጰያ የቻይናው አምባሳደር ዣሆ ዢያን ኢትዮጵያ ቻይና በኮቪድ19 በተጠቃች ጊዜ ወዳጅነቷን ያሳየች ጠንካራ አጋር መሆኗን ተናግረዋል።

አምባሳደሩ በቀጣይም ቻይና መሰል ድጋፎችን ታደርጋለችም ነው ያሉት፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ቻይና ዛሬ ካደረገችው ድጋፍ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም የኮቪድ19 መከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጓን አስታውሰዋል፡፡

ዛሬ የተደረገው ድጋፍም ሃገሪቱ የጀመረችውን የክትባት ሂደት ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል።

ሚኒስትሯ አሁን ላይ ያለውን ስርጭት ለመግታት ክትባት ብቻውን በቂ ስላልሆነ ህብረተሰቡም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!