የሀገር ውስጥ ዜና

306 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ

By Meseret Awoke

March 30, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት 306 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ጂዳ ከተማ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት በተለያዩ ሃገራት በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው ለማስመለስ ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!