የሀገር ውስጥ ዜና

የጤና ሚኒስቴር የብቃት ምዘና ፈተና መስጠት ጀመረ

By Tibebu Kebede

March 29, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር የብቃት ምዘና ፈተና መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ፈተናው በህክምና፣ ነርሲግ፣ ጤና መኮንን፣ አኒስቴዥያ ፣ ሜዲካል ላቦራቶሪ ቴክኖሎጅ፣ ፋርማሲ እና ሚድዋይፈሪ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ ባለሙያዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የብቃት ምዘና ፈተና መስጠት ጀምሯል፡፡

ፈተናው በመላ ሀገሪቱ በተዘጋጀ 38 የፈተና መስጫ ጣቢያዎች የሚሰጥ ሲሆን የፈተና አሰጣጥ ስርአቱን የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ አለምፀሀይ ጳውሎስ እና የሀገር አቀፋ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ከመፈተኛ ጣቢያዎች አንዱ በሆነው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በመገኘት ጎብኝተዋል፡፡

የብቃት ምዘና ፈተና የሚወስዱ 18 ሺህ 926 ተመዛኞች ሲሆኑ ጤና ባለሙያዎች አገልግሎት መስጠት ከመጀመራቸው በፊት ብቃታቸውንና ክሎታቸውን ለመመዘን የሚሰጥ ፈተና ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!