የሀገር ውስጥ ዜና

የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ብሔራዊ የፖሊሲ ምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

By Tibebu Kebede

March 29, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ብሔራዊ የፖሊሲ ምክክር መድረክ መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

በምክክር ሂደቱ የፌደራል፣ የክልል እና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች ያሏቸውን መልካም ተሞክሮዎች አካፍለዋል።

መድረኩ የበለጠ መጠናከር ያለባቸውን እንዲሁም በቀጣይነት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በመለየት እና በተቀናጀ መልኩ ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰበት ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!