አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ።
በስምንት ወራቱ ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 55 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር መገኘቱ ታውቋል፡፡
የወጪ ንግዱን ዕቅድ 82 በመቶ ማሳካት የተቻለ ሲሆን ከ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 1 ነጥብ 81 ቢሊየን ዶላር ጋር ሲነጻጸር የ16 በመቶ ወይም የ290 ሚሊየን ዶላር ብልጫ ገቢ መመዝገቡ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!