አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የ2013 ሶፊ ማልት ቅድሚያ ለሴቶች የሩጫ ውድድር ኮሮና ቫይረስን ከግምት ውስጥ በማስገባት ተካሄደ፡፡
ውድድሩ 5 ኪሎ ሜትር የሸፈነ ሲሆን የሴቶች ስኬትን እናክብር በሚል መሪ ቃል ነው ለ18ኛ ጊዜ የተካሄደው፡፡
መነሻውንም መድረሻውንም አትላስ መብራት ያደረገው ቅድሚያ ለሴቶች የሩጫ ውድድር የኮሮና ቫይረስን ከግምት ውስጥ በማስገባት መካሄዱ ተገልጿል፡፡
በዚህም ለተሳታፊዎች የሙቀት ልኬት መደረጉ እንዲሁም ሳኒታይዘር መቅረቡ ተሳታፊዎችም ርቀታቸውን ጠብቀው ሩጫውን ተሳትፈዋል፡፡
5 ኪሎ ሜትር በሸፈነው ሩጫ አትሌት ፋንታዬ በላይነህ በቀዳሚነት ውድድሩን ስታጠናቅቅ አትሌት መድኅን ገብረ ሥላሴናአትሌት ፈታው ዘርዓይ ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
ለአሸናፊዎችም ከ50 ሺህ እስከ 10 ሺህ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በዘላለም ተፈሪ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!