ዓለምአቀፋዊ ዜና

በግብጽ በባቡር አደጋ በጥቂቱ 32 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ

By Tibebu Kebede

March 27, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብጽ በባቡር አደጋ በጥቂቱ 32 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ፡፡

አደጋው ሁለት የመንገደኛ ባቡሮች ታህታ በተባለችው ከተማ ተጋጭተው የደረሰ ሲሆን፥ 165 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል ሲ ሲ ከአደጋው ጋር በተያያዘ ተጠያቂ በሚሆኑ አካላት ላይ ጠንካራ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡

በግብጽ ከባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ ጥራት ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ የባቡር አደጋዎች ይከሰታሉ፡፡

በሃገሪቱ በፈረንጆቹ 2002 በባቡር ላይ በተነሳ እሳት 373 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!