አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ኮትዲቯር አቢጃን ደርሰዋል።
ዋሊያዎቹ ከ5 ሰዓት የአየር በረራ በኋላ አቢጃን አየር ማረፊያ ሲደርሱ በኮትዲቫር የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሙሉጌታ እና በኤምባሲው ሰራተኞች እንዲሁም በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአቢጃን ተወካዮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ብሔራዊ ቡድኑ በአቢጃን ሴን ሆቴል ማረፊያውን ማድረጉን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በመጪው ማክሰኞ ከኮትዲቫር ብሄራዊ ቡድን ጋር ይጫወታሉ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን