የሀገር ውስጥ ዜና

299 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

By Tibebu Kebede

March 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 299 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ጂዳ ከተማ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት በተለያዩ ሃገራት በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው ለማስመለስ ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!