ስፓርት

የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌዴሬሽን አጠቃላይ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

By Meseret Demissu

March 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  “የዩኒቨርስቲ ስፖርት ዓለምን ለመቀየር” በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌዴሬሽን አጠቃላይ ስብሰባ በኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤና የተለያዩ ከአፍሪካ ሀገራት የመጡ የፌዴሬሽኑ አባላት ተገኝተዋል።

ስፖርትን ለአብሮነትና ትብብር በማዋል የአፍሪካንና የአፍሪካውያንን ህይወት ወደ ተሻለ ደረጃ ለመቀየር መጠቀም ይገባል ተብሏል።

ስፖርት የሀገርን ገፅታ ከመገንባት ባሻገር መሪነትን በተግባር ትውልድ ውስጥ ማስረፅ የሚቻልበት አንዱ መንገድ በመሆኑ በዚህ ላይ በአፍሪካ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መስራት ይገባቸዋልመባሉን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!