Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልዑክ በሻሸመኔ ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና በከተማ ልማት አስተባባሪ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ የልዑካን ቡድን በሻሸመኔ ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን ጎበኘ፡፡
በጉብኝቱ ከወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በተጨማሪ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት እና ፖለቲካ ሃላፊ አቶ ሳዳት ናሻን ጨምሮ የተለያዩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ቡድኑ በከተማው በ38 ሚሊየን ብር እየተገባ የሚገኘውን የመጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክትንም ጎብኝቷል፡፡
በሻሸመኔ ከተማ ከዚህ በፊት በሶስት ፓምፖች ሲሰጥ የነበረው የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ወደ 10 ፓምፖች ማደጉ ተገልጿል፡፡
በከተማው የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋኑ 45 በመቶ የነበረው ወደ 60 በመቶ ማደጉም ነው የተገለጸው፡፡
በጉብኝቱ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በማንኛውም አገልግሎት የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማርካት በሃላፊነት እና በታማኝነት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በጂብሪል ሃሰን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version