የሀገር ውስጥ ዜና

እነ አቶ ስብሃት ነጋ ያቀረቡት ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳ ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

By Tibebu Kebede

March 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እነ አቶ ስብሃት ነጋ ያቀረቡት ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳ ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ባሳለፍነው ሳምንት የጊዜ ቀጠሮ ጉዳያቸውን የተመለከቱት ዳኛ ገለልተኛ ሆነው ስለማይመለከቱልን ከመዝገቡ ይነሱልን ሲሉ ማመልከታቸው ይታወሳል፡፡

ይሁንና በፍርድ ቤቱ ጉዳዩ ተመርምሮ ዳኛው የጊዜ ቀጠሮ ጉዳዩን ሲመለከቱ ገለልተኛና ፍትሃዊ ሆነው ሲዳኙ እና ካለማንም ጫና ጉዳያቸውን ሲመለከቱ እንደነበር ፍርድ ቤቱ መርምሮ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል፡፡

ለዚህም በዋናነት እነ አቶ ስብሃት ዳኛው በጊዜ ቀጠሮው መዝገብ ላይ ገለልተኛ ሆነው እንዳላዩላቸው በማስረጃ ያልተደገፈና በጭፍን ጥያቄ አቅርበዋል በሚል ነው ውድቅ ያደረገው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ይቀየርልን ብለው ላቀረቡት ማመልከቻ ጉዳዩ አስተዳደራዊ ጉዳይ በመሆኑና ክርክር የሚደረግበት ባለመሆኑ ይህ ጥያቄ መቅረብ ካለበትም ስልጣን ላለው ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው በሚል አልተመለከተውም፡፡

ይሁንና በቀጣይ የዐቃቤ ህግን የቅድመ መርምራ ምስክር ሂደቱን በሚመለከተው ዳኛ ላይ በሌላ ዳኛ አስተያየት ተሰጥቶበት እስከሚቀርብ ድረስ በቀጣይ በፅህፈት ቤት ቀጠሮ ይሰጣል ተብሏል፡፡

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!