ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፋኦ በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መንጋ መቀነሱን አስታወቀ

By Tibebu Kebede

March 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መንጋ መቀነሱን አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያና ኬንያን ጨምሮ በቀጠናው የዝናብ አለመኖር ለበረሃ አንበጣው መቀነስ ምክንያት መሆኑን ገልጿል፡፡

በአካባቢው ያለው ዝቅተኛ የዝናብ መጠን ከሚደረገው ቁጥጥር ጋር ተያይዞ የአንበጣ መንጋው እንዳይፈለፈል አድርጎታልም ነው ያለው፡፡

ዝናብ አምጭ ሁኔታዎች ካለመስተዋላቸው ጋር ተያይዞ ሁኔታዎች በዚሁ ሊቀጥሉ እንደሚችሉም ነው የገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈ ግን የአንበጣ መንጋውን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ቁጥጥር ማጠናከር እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

አሁን ላይ በኬንያ አንዳንድ አካባቢዎች እና በታንዛኒያ ድንበር አካባቢ ኩብኩባ መታየቱንም ጠቅሷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!