ኮሮናቫይረስ

በኢትዮጵያ ከሦስት ግለሰቦች አንደኛው ኮቪድ-19 ሊኖርበት ይችላል – የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

By Abrham Fekede

March 25, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ከሦስት ግለሰቦች አንደኛው የኮሮና ቫይረስ ሊገኝበት እንደሚችል የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱንም ጠቅሷል፡፡

በትናንትናው ዕለት ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች መካከል 26ቱ ኮቪድ እንደተገኘባቸው አሳይቷል፡፡

ይህ ማለት አብረውን ካሉ ሶስት ግለሰቦች አንዱ የኮሮና ቫይረስ ሊገኝበት እንደሚችል ማሳያ መሆኑን ነው ኢንስቲትዩቱ ያስታወቀው፡፡

በእያንዳንዱ ከተሞችና ክልሎች ውስጥ ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች መካከል በአዲስ አበባ 25ቱ፣ በኦሮሚያ 42ቱ፣በድሬዳዋ 43ቱ፣በሲዳማ 67ቱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በትናንትናው ዕለት ብቻ 752 ግለሰቦች ፅኑ ህሙማን ክፍል ገብተዋል፡፡

ከነዚህ መካከል ደግሞ 94 ግለሰቦች በሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ እየተነፈሱ የሚገኙ ናቸው ተብሏል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የነበረው ከፍተኛ የታማሚ ቁጥር 81 እንደነበርም ኢንቲትዩቱ አስታውሷል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ወደ ህክምና ማዕከል ከሚገቡት 100 ግለሰቦች ውስጥ 79 የሚሆኑት በተለያየ መጠን ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው መሆናቸውንም ገልጿል፡፡

ኢንስቲትዩት ከሦስት ሰዎች አንዱ በወረርሽኙ ሊያዝ እንደሚችል ግምት ውስጥ አስገብቶ ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ጥንቃቄ እንዲያደርግና የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብር ጥሪውን አቅርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን