አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሠ ወቅታዊ የኮቪድ 19 ሥርጭትና እንደ ሀገር እያደረሠ ስላለው ተጨባጭ ጉዳት አስመልክቶ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ጋር ተወያዩ።
የኮቪድ 19 እንደ ሀገር የከፋ ጉዳት እያደረሠና በተለይም የጽኑ ሕሙማን ተጠቂዎች ቁጥር በአገሪቱ ካለው የጽኑ ሕሙማን የማስተናገድ አቅም አንፃር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ከመሆኑም በላይ በያዝነው ወር ብቻ በጤና ተቋም ደረጃ ከፍተኛው የሞት መጠን እንደተመዘገበም ተገልጿል።
በመሆኑም የሃይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸው እራሳቸውን እንዲጠብቁ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል በአገባቡ እንዲያደርጉ እና በየትኛውም ሁኔታ ሲገኙ አካላዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ ማስተማር እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ለአምልኮ በሚመጡ አማኞች ሁሉ በየቤተ-እምነቱ ተፈፃሚ እንዲሆኑ ያወጧቸው ደንቦች እንዲከበሩም ጠይቀዋል።
የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶችም ስርጭቱን ለመከላከል አስፈላጊውን መመራያ በየተቋማቸው እንደሚሠጡ ማሳወቃቸውን ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን