አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሽረ እንዳስላሴ ከተማና አካባቢው የተፈጠረው ሰላምና መረጋጋት ዘላቂ እንዲሆን ነዋሪዎች ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በትብብር እየሰሩ መሆኑን ገለጹ።
የከተማዋ ነዋሪዎች በህወሓት ጁንታ ላይ የህግ ማስከበር እርምጃ ከተወሰደ ወዲህ ከተማዋ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሷን ነው የተናገሩት፡፡
የህወሓት ጁንታ ታጣቂ ሃይል በሰሜን ዕዝ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ባደረሰው ጥቃት መንግስት የህግ ማስከበር እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል።
በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ከተካሄደባቸው አካባቢዎች የሰሜን ምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች ሽረ ከተማ አንዷ ስትሆን አሁን ላይ በከተማዋ ነዋሪዎች በሰላም የየእለት ስራቸውን በማከናወን ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ከሃገር መከላከያ ሰራዊትና ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በመሆን በአካባቢው ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር መስራታቸውን ገልጸዋል።
በአካባቢው አልፎ አልፎ የስርቆትና ዘረፋ ወንጀል ስለሚስተዋል ለጋራ ደህንነታቸው ከፀጥታ ሃይሉ ጋር አብረው እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።
የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አረጋይ በበኩላቸው የዞኑን ሰላም ለማስጠበቅ ከህብረተሰቡና ከጸጥታ አካላት ጋር በጋራ እየሰራን ነው ብለዋል።
ከተማዋ ጊዜያዊ አስተዳደር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማደራጀት ሰላምና ጸጥታ የማስፈን ስራ በማከናወኑ ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱንም ማረጋገጣቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን