Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ያገባኛል (አይ ኬር) ስትራቴጂካዊ እቅድ ፕሮግራም የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በድሬዳዋ ድል ጮራ ሆስፒታል ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ የተመራ የልዑካን ቡድን በ1954ዓ.ም የተመሠረተውን የድል ጮራ ሆስፒታል ጎብኝቷል፡፡
በጉቡኝቱ ስለ ያገባኛል (አይኬር) ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ማብራሪያ በኢኒሼቲቭ ባለሙያዎች ተሰጥቷል።
የድል ጮራ ሆስፒታል ዋና የስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሙና ኢብራሂም ፕሮግራሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚተገበርባቸው 24 ሆስፒታሎች ውስጥ አንዱ ድል ጮራ በመሆኑ የጤና ተቋሙ በዘርፉ ያጋጠሙትን ችግሮች ለመቅረፍ እንደሚያስችለዉ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል።
የድል ጮራ ሆስፒታል ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሱልጣን አሊዪ በበኩላቸው ሆስፒታሉ ከድሬዳዋ ባሻገር ለአብዛኛው የምስራቅ ሐረርጌ ነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ለአዲሱ የአይ ኬር ዕቅድ ተግባራዊነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።
በመጪዎቹ ሁለት አመታት በ517 ሚሊየን ብር በሆስፒታል የሚተገበረው ይህ አሰራር በጀቱ ጤና ሚኒስቴርን ጨምሮ በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እንደሚሸፈን ታውቋል፡፡
ከዚህም ውስጥ 50 በመቶው በጤና ሚኒስቴር ፣30 በመቶው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ በድል ጮራ ሆስፒታል ውስጣዊ በጀት እንደሚሸፈን የሆስፒታሉ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ታደሰ አስታውቀዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version