Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢዜማ የምርጫ ማኒፌስቶውን ለህዝብ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የምርጫ ማኒፌስቶውን ለህዝብ ይፋ አድርጓል፡፡
ማኒፌስቶው ለማዘጋጀት ላለፉት 2 ዓመታት ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱ ተገልጿል፡፡
ሰነዱ በሀገር ደህንነት እንዲሁም በፓለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች ያሉ መሰረታዊ ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በግልፅ ያስቀመጠ ስለመሆኑም ተጠቅሷል፡፡
የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፓርቲው በመጭው ምርጫ ሀገር ለማስተዳደር ቢመረጥ ለቀጣይ 5 ዓመታት በስራ ላይ የሚውል እና የገባውን ቃል ካልተገበረ ተጠያቂ የሚሆንበትን ሰነድ ማዘጋጀቱን መግለፃቸው ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version