Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአርባ ምንጭ ከተማ ሲኤቻ ገበያ የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርባ ምንጭ ከተማ ሲኤቻ ገበያ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የተከሰተው የእሳት አደጋ የአካባቢው ህብረተሰብ ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ በቁጥጥር ሥር ሊውል መቻሉ ተገለፀ፡፡
የእሳት አደጋው ትናንት ምሽት 3 ሰዓት አከባቢ በአርባ ምንጭ ከተማ ሲኤቻ ገበያ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የተከሰተው ሲሆን የጉዳቱ መጠንና የአደጋው መንስኤም እየተጣራ መሆኑ ታውቋል፡፡
የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ሃላፊ መቶ አለቃ ሀይለሚካኤል ጉላንታ እሳቱን ለማጥፋት የሲኤቻ ወጣቶችና ህብረተሰቡ ላደረገው ከፍተኛ ርብርብ ፣የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ላሳየው አጋርነት እንዲሁም የአርባ ምንጭ አውሮፕላን ማረፊያ የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና ላደረገው ትብብር ምስጋና ማቅረባቸውን ከአርባምንጭ ከተማ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version