አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ በአንድ ሳምንት ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ምርምራ ከተደረገላቸው 380 ሰዎች ውስጥ 125 ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተገለጸ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የጤና ቢሮ ኃላፊዋ አሁን ላይ በከተማዋ የኦክስጅን እጥረት ገጥሞናል ብለዋል፡፡
በየቀኑ ከ10 እስከ 15 የሚሆኑት ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸውን ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ በአንድ ሳምንት ውስጥ ሦስት ሰው በቫይረሱ ምክንያት ህይወቱን አጥቷል፡፡
የመንግስትና የግል ህክምና ተቋማት ተቀናጅተው በማስተናገድ ላይ እንደሚገኙም በመግለጫቸው ጠቅሰዋል፡፡
የህግ አስፈጻሚ አካላት ቫይረሱን ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎችን እንዲያጽፈጽሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የጤና ቢሮ ኃላፊዋ ወይዘሮ ለምለም ህብረተሰቡ ስርጭቱን ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዙፋን ካሳሁን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን