ቢዝነስ

የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርቱን ለገበያ ማቅረብ ጀመረ

By Tibebu Kebede

March 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ባለፉት አራት ወራት ስራ አቁሞ የነበረው ትግራይ ክልል የሚገኘው መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርትን ለገበያ ማቅረብ መጀመሩን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል አስታወቁ፡፡

ፋብሪካው ወደ ማምረት በመመለስ ምርቱን ለገበያ ማቅረብ መጀመሩ ለሲሚንቶ ዋጋ መሻሻል አወንታዊ ሚና ይኖረዋል ያሉት ሚኒስትሩ ለዘርፉ የዋጋ መሻሻል ሁሉም የበኩሉን ሀገራዊ ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በህገ ወጥ ደላሎች የምርት መሰወር ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ የአንድ ኩንታል የሲሚንቶ ዋጋ እስከ 600 መቶ ብር ደርሶ እንደነበር በማስታወስም፥ ጥብቅ የቁጥጥርና ክትትል ስራ በመስራት የመሸጫ ዋጋውን ወደ 420 ብር መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርት መጠናቸውን በመጨመር በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሲሚንቶን ምርት የመሸጫ ዋጋ ተመጣጣኝ እንዲሆን ለማድረግ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ውጤት ማምጣቱን ጠቅሰው፥ በፍላጎትና አቅርቦት መካከል ያለውን ክፍተት ለማስተካከል እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!